በልደታ manufacturing college ለብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ 456 ሰልጣኞች ተመረቁ።
ሰልጣኞት ከወረዳ 5 እና ከወረዳ 3 የተመለመሉ ሲሆኑ በልደታ ማኒፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለተከታታይ 10 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና ወስደው በአግባቡ በማጠናቀቃቸው ዛሬ ተመርቀዋል።
ለሰልጣኞች ወደ ስራ ላይ ልምምድ ለመግባት የሚጠበቅባቸውን ተግባራት ተብራርቶላቸዋል።
456 ሰልጣኞች ውስጥ ብቃቱን አሟልተው የሚመለመሉት ለ6 ወራት የስራ ላይ ልምምድ ከኢንዱስትሪዎች ጋር እንደሚተሳሰሩም ተገልጿል።
ሰልጣኞች ስልጠናው ለህይወታችን እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉ ሲሆን ስልጠናው ትኩረት ተሰጥቶበት መሰልጠናቸውንም ተናግረዋል።
.