Home የአምራችነት ቀን

የአምራችነት ቀን

18th June, 2024

ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የአምራችነት ቀንን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አከበረ

ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም

ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የአምራችነት ቀንን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል፡፡

ኮሌጁ ቀኑን ምክንያት በማድረግ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ  የለማ የጓሮ  አትክልቶችን የመንከባከብና የመሰብሰብ እንዲሁም ቴክኖሎጂዎችን የማሻሻል መርሃ ግብር አከናውኗል፡፡

በመርሀ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ  ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሪት ፀዳለ  ተክሉ ሴክተሩ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በስልጠናና በቴክኖሎጂ አምራቾችን የሚያበረታታ በመሆኑ የማምረት አቅምን በማሳደግ ራሳችንን ብሎም ሀገራችንን በሁሉም ዘርፍ ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተኩ ታዬ በበኩላቸው ኮሌጁ ቀኑን ለማሰብ የጓሮ አትክልቶችን በመንከባከብ በወርክ ሾፓች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የማሻሻል ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡በአምራችነት ቀን የሚመረቱ ምርቶችም ኮሌጁን ሊጠቅሙ የሚችሉ  ብሎም የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት የሚፈቱ መሆናቸውንና በበአላት ሰሞን ብቻ ሳይሆን ዘወትር የሚከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን ዋና ዲኑ አክለው ገልፀዋል፡፡ በተለያዩ ተግባራት ታስቦ የሚውለው አምስቱ  የጳጉሜ ቀናት በቀሪዎቹ ቀናትም በተለያዩ ተግባራት ታስቦ የሚውል  ይሆናል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with